Metro (ሜትሮ)—የእንቅስቃሴዎ ኤጄንሲ

የKing County Metro(ኪንግ ካውንቲ ሜትሮ)ጤናማ ማህበረሰብን፣ የሚያድግ ኢኮኖሚ፣እና ዘላቂ አካባቢ ለመገንባት የሚረዳ ሰፊ ተደራሽነት ያለው እና የፈጠራ መፍትሄዎች ያሉት በአለም ምርጥ፣የተቀናጀ የህዝብ ማጓጓዣ መረብ እየፈጠረ ነው።

እንቅስቃሴ ሰብዓዊ መብት ነው

ለMetro(ሜትሮ)፣እንቅስቃሴ ማለት መሄድ ወደሚያስፈልግዎ ቦታ፣በሚያስፈልግዎ ጊዜ-በአስተማማኝ ሁኔታ፣ፍትሀዊ፣እና ዘላቂ በሆነ መልኩ መሄድ ማለት ነው።

ተልኮአችን

የኛ ተልእኮ በKing County(ኪንግ ካውንቲ)አህጉራዊ እንቅስቃሴ እና የህይወት ጥራትን ለማሻሻል ተመራጭ የህዝብ ማጓጓዣ አገልግሎቶችን ማቅረብ ነው።

የክንግ ካውንቲ ማህበረሰቦችና መልከአ ምድር ስብጥር ናቸው ፣ ስለዚህ እኛ ሰዎችን ከእድሎች የሚያገናኝና እያደጉ የሚገኙትን ማህበረሰቦች የሚያጣምር የእንቅስቃሴ መረብ እየቀየስን አለን ፡፡ እኛ በዘርና በቦታ ላይ የተመሰረቱ ልዩነቶችን ለማጥፋት፣ እና ፍላጎቶች ከሁሉ እጅግ በሚበልጡበት ቦታዎች ለማስቀደም ቆርጠን ተነስተናል፡፡

እኛ በአህጉሩ ትልቁ የባስ መረብ ነን፣እና wየአየር ጥራታችንን ለመጠበቅ የተበከለ አየር ፍሰትን እየቀነስን ነው። Metro የትራንዚት ኢንዱስትሪውን እየመራ ነው—እና አገሩን—በ2040 ወደ 100% የዜሮ-ፍሰት እየተጓዘ ነው።

የሚያድገውን አህጉራችንን የሚያድገውን የአገልግሎት ፍላጎቶች ለማሟላት፣ አሁን ያለውን የባስ መቆሚያዎችን እናሻሽላለን እና አዳዲሶችንም እንሰራለን። የMetro(ሜትሮ) አገልግሎቶች ከከፍተኛ አረንጓዴ ግንባታ እና ዘላቂ የእድገት ልማዶች ጋር በሚጣጣም መልኩ ይገነባል፣እና ለአካባቢው የስራ እድሎችን ያቀርባል።

ሊኖርበት የሚችል ማህበረሰቦችን፣ የሚያድግ ኢኮኖሚ፣እና ዘላቂ አካባቢ የሚደግፍ የእንቅስቃሴ መረብ በመስራት፣ ሁላችንም አብረን ወደፊት መጓዝ እንችላለን።


በጀት

ለእርስዎ ተመራጭ የህዝብ ማጓጓዣ አገልግሎቶች ማቅረብ እና የአህጉራዊ እንቅስቃሴዎ ን ማሻሻል የኛ የማይታክት ስራ ነው።

Metro(ሜትሮ) ገንዘብ እንዴት እንደሚያገኝ

52% የሽያጭ ታክስ

15% የጉዞ ዋጋዎች*

15% አህጉራዊ አጋሮች

8% ሌላ

6% የገንዘብ እርዳታዎች

4% የእዳ ሰነዶች

ገንዘብ እንዴት ወጪ እንደሚሆን

73% የስራ ወጪ

14% ዋና ገንዘብ—መሰረተ ልማት

11% ዋና ገንዘብ-መርከብ

2% የብድር አገልግሎት